Find Posts By Topic

በሲያትል ውስጥ ደህንነታቸው የተጠበቀ ማህበረሰቦችን ለመደገፍ አዲስ የገንዘብ ድጋፍ ዕድል

Photo by Serge van Neck on Unsplash

ከጆርጅ ፍሎይድ ሞት በኋላ በፖሊስ ጭካኔ ላይ የተቃውሞ ሰልፎች በተለይም በጥቁር ማህበረሰቦች ውስጥ በመላው አሜሪካ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተሰራጭተዋል። ልክ እንደ ብዙ ከተሞች ሁሉ በብዙ ዘር እና ከብዙ ባህላዊ ጥምረት ጋር የሚሰሩ በጥቁር አደራጆች የሚመራው ብጥብጥን ለማስቆም የዘር ፍትህ እና የማህበረሰብ መር መፍትሄዎች ጥሪ በሲያትል ውስጥ ከሚካሄዱት ጥረቶች ጋር ድምፃቸውን አሰምተዋል። በዚህ አደረጃጀት የህብረተሰቡን ደህንነት እንደገና ለማሰብ የገንዘብ ድጋፍን ለማሳደግ የሚያስችል ሕግ በሲያትል ተላለፈ።

የሲያትል የሰብአዊ አገልግሎት መምሪያ (Seattle Human Services Department (HSD)) የ2021 የማህበረሰብ ደህንነት አቅም ግንባታ የፕሮፖዛል ጥያቄ (Community Safety Capacity Building Request for Proposals (RFP)) አመጽን ለማስቆም ከሚሰሩ በማህበረሰብ ከሚመሩ ቡድኖች እና በጥቁር፣ በአገሪቱ ተወላጅ እና ቀለም ባላቸው ሰዎች (BIPOC) በሚመራው ማህበረሰብ ውስጥ ደህንነትን እንደገና ለማሰብ በጥቁር፣ በአገሪቱ ተወላጅ ፣ በላቲንክስ፣ በፓስፊክ ደሴት፣ እና በስደተኞች እና በስደተኞች ማህበረሰቦች ላይ የተወሰነ ትኩረት በመስጠት ማመልከቻዎችን እየፈለገ ነው። የዚህ የገንዘብ ድጋፍ ዓላማ አመፅን ለማስቆም እና ደህንነትን ለመጨመር በማኅበረሰብ መሪነት መፍትሔዎች ላይ የሚሰሩ ቡድኖችን አቅም መገንባት ነው።

የማህበረሰብ ደህንነት አቅም ግንባታ RFP ከጁላይ 1፣ 2021 እስከ ዲሴምበር 31፣ 2022 ባለው ጊዜ ውስጥ በአንድ ጊዜ የገንዘብ ድጋፍ በግምት $10,400,000 ኢንቨስት እያደረገ ነው። የተጠናቀቀ ማመልከቻን የማስገቢያ ቀነ-ገደብ አርብ፣ ኤፕሪል 9፣ 2021ከሰአት 12:00 (እኩለ ቀን) ነው። ይህ RFP ደረጃውን ለጠበቀ HSD ኤጄንሲ አነስተኛ የብቃት መስፈርቶችን እና በእነዚህ መመሪያዎች ውስጥ በአራተኛ ክፍል ውስጥ ለተዘረዘረ ማንኛውንም ተጨማሪ መስፈርት ለሚያሟሉ ድርጅቶች ክፍት ነው። ድርጅትዎ አነስተኛውን የብቁነት መስፈርቶችን የማያሟላ ከሆነ መስፈርቶቹን የሚያሟላ የፊስካል ስፖንሰር ማግኘት ይፈቀዳል። የፊስካል ስፖንሰር መስፈርቶች በገንዘብ ድጋፍ ሂደት ሀብቶች ስርበገንዘብ ድጋፍ ገጽ ላይ ይገኛሉ። ሃላፊነታቸው የተወሰነ ኩባንያዎች (Limited Liability Companies LLCs) በዚህ RFP ውስጥ እንዲያመለክቱ ተፈቅዶላቸዋል። እስከ 40 የሚደርሱ ሀሳቦች የገንዘብ ድጋፍ ሊያገኙ ይችላሉ።

ሁከት ማቆም እና ወንጀል መቀነስን ጨምሮ ለደህንነት ሁኔታዎችን ለመፍጠር የሚሰሩ ሁሉም ድርጅቶች እንዲያመለክቱ የተበረታቱ ሲሆን በጥቁሮች፣ በአገሪቱ ተወላጆች፣ በላቲኖች፣ በፓሲፊክ ደሴት ለሚኖሩ እና በስደተኞች ለሚመሩ የህብረተሰብ ቡድኖች በዘረኝነት፣ የጭቆና ስርዓቶች እና በአመፅ እና በወንጀል የህግ ስርዓት ላይ የሚደርሰው ጉዳት ዋና ተጠቂ በመሆናቸው ቅድሚያ ይሰጣቸዋል።አገልግሎቶች በሲያትል ውስጥ መከናወን አለባቸው።

አነስተኛውን ብቃት ያሟሉ ሁሉም ድርጅቶች ቃለ መጠይቅ ይደረግላቸዋል። የቃለ መጠይቅ ጥያቄዎች እና መመዘኛዎች ቃለ-መጠይቅ ከታቀደበት ጊዜ ቢያንስ ከአንድ ሳምንት በፊት ይቀርባሉ።

የRFP ሁሉም ቁሳቁሶች እና ዝመናዎች በHSD የገንዘብ ድጋፍ ዕድሎች ድረ ገጽ ላይ ይገኛሉ። HSD የተደረጉ ለውጦች ላይ ለእያንዳንዱ ግለሰብ ማሳወቂያ አይሰጥም፣ እና ድርጅቶች ማንኛውንም ለውጥ ለማጣራት ይህን ድረ-ገጽ በመደበኛነት የመከታተል ኃላፊነት አለባቸው። HSD ማመልከቻዎቻቸውን በሚዘጋጁበት ጊዜ በHSD የተጠየቀውን መረጃ በማቅረብ ወይም በምርጫው ሂደት ውስጥ በመሳተፍ ላይ ለሚወጣ ማንኛውም ወጪ HSD አይከፍልም።

አንዳንድ የትርጉም ማቴሪያሎችን ማግኘት ይችላሉ።

ጥያቄ ካለዎት እባክዎ የሚከተለውን ያነጋግሩ: ናታሊ ቶምሰን፣ የገንዘብ ድጋፍ ሂደት አስተባባሪ፣ በ natalie.thomson@seattle.gov.